XtGem Forum catalog
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

.:☀:አስተማሪ ታሪክ ለኛ
እውነትን መናገር:☀:.


Tumblr mk31ktfFhi1rc53xvo1 500

እውነትን መናገር በጣም የሚወደድ መልካም ልማድ ነው። ሁልጊዜም እውነትን የምንናገር ከሆነ እራሳችነን ከብዙ ችግሮች መጠበቅ እንችላለን። ይህ ብዙ መጥፎ ነገሮችን የሰራ ሰው ታሪክ ነው። ነገር ግን እውነትን ለመናገር ቃል በመግባቱ ከመጥፎ ነገር ጠብቆታል።

አንድ ጊዜ አንድ ሰው ወደ ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) መጣና እንዲህ አላቸው: የአሏህ ነብይ ሆይ ብዙ መጥፎ ልማዶች አሉብኝና መጀመሪያ የትኛውን መተው አለብኝ? ሲል ጠየቃቸው። ነብዩም ውሸት መናገርን በመጀመሪያ ተው አሉት።

ሰውየውም ይህን እንደሚያደርግ ቃል ገብቶላቸው ወደ ቤቱ ሄደ። በምሽት ሊሰርቅ ሊሄድ ነበርና ከመሄዱ በፊት ለተወሰነ ጊዜ ከነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ጋር የገባውን ቃልኪዳን አሰበ። ነገ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) የት ነበርክ? ብለው ቢጠይቁኝ ምን እላለሁ ልሰርቅ ሂጄ ነበር እላቸዋለሁ? አይሆንም እንዲህማ ልላቸው አልችልም፤ እንዲሁም ልዋሻቸው አልችልም። እውነቱን የምናገር ከሆነ ሰዎች እኔን መጥላት ይጀምራሉ፤ ሌባ ብለውም ይጠሩኛል። በመስረቄም እቀጣለሁ አለ።

ሰውየው በዚያን ለሊት ላለመስረቅ ወሰነና ይህን መጥፎ ልማዱን ተወ። በቀጣዩ ቀን ወይን(አስካሪ መጠጥ) ለመጠጣት ፈልጐ ይህን ለማድረግ ባሰበ ጊዜ ለራሱ እንዲህ አለ:- ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) በዚህ ቀን ምን አደረክ ብለው ቢጠይቁኝ ምን እላቸዋለሁ ልዋሽ አልችልም ደግሞ እውነታውን ብናገን ሰዎች ይጠሉኛል። ምክኒያቱም ሙስሊም ወይን (አስካሪ መጠጥ) መጠጣት አይፈቀድለትም። እናም ወይን(አስካሪ መጠጥ) የመጠጣት ሀሳብን(ፍላጐቱን) ተወ። በዚህ መንገድ ሰውየው መጥፎ ነገሮችን ለመስራት ባሰበ ጊዜ እውነትን ለመናገር የገባውን ቃል ኪዳን ያስታውሳል። እያለያለ አንድ በአንድ መጥፎ ልማዶቹን ሁሉ ተወ። ጥሩ ሙስሊምና ጥሩ ሰው ሆነ።

ሁልጊዜም እውነትን የምንናገር ከሆነ ጠንካራ ሙስሊም መሆን እንችላለን። የአሏህ ውዴታን ያስገኝልናል። የአሏህን ውዴታ ካገኘን አሏህ በጀነት ይመነዳናል።


©የወጣቱ ተልእኮ

۩Youth-Mission
የወጣቱ ተልእኮ-> page۩

page:
http://facebook.com/youth.mission29

website:
http://youth-mission.mobie.in

'~'-.,__,.-'~'
_,.-'~''~'-.,_

746

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ